የአብደላህ ኢብኑ ኡሚ መኩም ቁርአን ማህበር  ሃይማኖታዊ ግብረሰናይ ድርጅት ሲሆን ለሙስሊም አካል ጉዳተኛ እህት እና ወንድሞች ኢስላማዊ ትምህርቶችን ለማሰራጨት ያለመ ነው ፡፡ አብደላህ ኢብኑ ኡሚ መክቱም የቁርአን ማህበር ከተመሰረተበት ከ 2010 አ.ል ጀምሮ ለሙስሊም አይነ ስውራን  የብሬል ቁርአንን በማስተማር እና ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የብሬል   ቁርኣንን በማሰራጨት ላይ ሲሆን  በተጨማሪም መስማት ለተሳናቸው እህት እና ወንድሞች የምልክት ቋንቋን በማስተማር ዲናዊ እውቀታቸውን እንዲያዳብሩ ከፍተኛ ስራ በመስራት ላይ ይገኛል ፡፡

ራእያችን በምስራቅ አፍሪካ የአካል ጉዳተኞች መሪ ድርጅት ሆኖ መገኘት ነው፡፡አዲስ አበባ ከሚገኘው ዋና መስሪያ ቤት በተጨማሪ በሰበታ፣ጎንደር፣አዳማ፣ደሴ አና መካነ ሰላም ቅርንጫፎች አሉን፡፡በነዚህም ማእከላት ሙስሊም አይነ ስውራን  ከብሬል ቁርኣን ትምህርት በተጨማሪ መንፈሳዊ፣ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጠቀሜታን ያገኛሉ፡፡

 

Abdullah Ibn Umi Makum Qur’an Association is a religious humanitarian organization that aims to spread Islamic teachings to Muslim brothers and sisters with disabilities. Since the establishment of the Qur’an Association in 2018, has been doing a great job of teaching the Braille Quran to the blind Muslims and distributing the Braille Quran to different parts of the country, while also teaching sign language to the deaf sisters and brothers to develop their religious knowledge.

Our vision is to be a leading organization for people with disabilities in East Africa. In addition to the head office in Addis Ababa, we have branches in Sebeta, Gondar, Adama, Dese And Mekane Salam. In these centers, Muslim blind people get spiritual, economic and social benefits in addition to Braille Quran education. .

What we do

We are on Social media